ፈረሰኞቹ ከአምበላቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

ላለፉት 14 ዓመታት ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን ፈረሰኞቹን ያገለገለው አማካይ በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ለ2017 የውድድር ዘመን ከቡድኑ ጋር አብሮ በዝግጅት ላይ የነበረው እና ቡድኑን በአምበልነት እንደሚመራ ይጠበቅ የነበረው አማካይ ናትናኤል ዘለቀ በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

ስድስት የሊግ ዋንጫዎችን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ያነሳው ናትናኤል በ2003 ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ እሰከ ዋናው ቡድን ድረስ ለአስራ አራት ዓመታት የዘለቀ የስኬት ቆይታን ያደረገ ሲሆን የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት ቢኖረውም ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ እርግጥ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።