የዝውውር መስኮቱ ነገ ይዘጋል

ላለፉት ሦስት ወራት ክፍት የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የክረምት የዝውውር መስኮት ነገ ምሽት ይዘጋል።

ላለፉት ሦስት ወራት ተከፍቶ የቆየው የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የክረምት የዝውውር መስኮት ነገ ምሽት በይፋ ይዘጋል። ከጥቂቶቹ በስተቀር በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ አድርገው አዲስ ቡድን በመገንባት የውድድር ዓመቱን የጀመሩት የሊጉ ክለቦች ዝውውሮቻቸውን በነገው ዕለት የሚያገባድዱ ይሆናል።

አብዛኞቹ የሊጉ ክለቦች የተሻለ ቡድን ይዘው በውድድሩ ለመቅረብ ቀደም ብለው ዝውውሮቻቸውን ያገባደዱ ቢሆንም ጥቂት ክለቦች በቀሩት ሰዓታት አዳዲስ ተጫዋቾች ለማስፈረም በእንቅስቃሴ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።