የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ዛሬ ይጀምራል

በታንዛንያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከሀያ ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዛሬ ይጀምራል


የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ዋንጫ ከሀያ ዓመት በታች የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ በታንዛንያ ርዕሰ መዲና ዳሬ ሰላም ይጀምራል ፤ ዘጠኝ ሀገራት በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚወደዳሩበት እና ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዬቹ አስራ አራት ቀናት የሚከናወነው ይህ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ታንዛንያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ብሩንዲ ይሳተፉበታል።

ከቀናት በፊት ወደ ስፍራው ያቀናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ሰኞ መስከረም 27 የዩጋንዳ አቻውን በመግጠም ውድድሩን የሚጀምር ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላም በሁለተኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን እንዲሁም ጥቅምት 1 ላይ ደግሞ ብሩንዲን የሚገጥም ይሆናል። ውድድሩ አዘጋጅዋ ታንዛንያ ከ ኬንያ በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምር ሲሆን ወደ ፍፃሜ ያለፉ ሁለት ቡድኖችም ዞኑን ወክለው በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ይወዳደራሉ።