ስሑል ሽረዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል

በሊጉ መልካም አጀማመርን እያደረጉ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች የመስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።


በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በፕሪምየር ሊጉ መልካም አጀማመር ያደረጉት ስሑል ሽረዎች ራሳቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል ፤ ቡድኑን ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሰው ተጫዋች ደግሞ ሀብታሙ ገዛኸኝ ነው።

በደቡብ ፖሊስ በመቀጠል ደግሞ ለአራት ዓመታት በሲዳማ ቡና የተጫወተው ይህ የመስመር ተጫዋች በፋሲል ከነማ የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ ከቡድኑ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት በመለያየት በ2016 የወድድር ዘመን በቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና እየተጫወተ ቢቆይም የ2017 የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ መለያ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል።

ተጫዋቹ ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት ከደረሰ በኋላ በትናንትናው ዕለት የህክምና ምርመራው ያገባደደ ሲሆን በቀጣዮቹ ሰዓታት ዝውውር ይቋጫል ተብሎ ይጠበቃል።