ስሑል ሽረዎች አማካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ባለፈው የውድድር ዘመን በአዳማ ከተማ ቆይታ የነበረው አማካዩ ወደ ስሁል ሽረ አምርቷል።


በፕሪምየር ሊጉ መልካም አጀማመር በማድረግ በአምስት ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ስሑል ሽረዎች አማካዩ  ዊልያም ሰለሞንን የግላቸው ለማድረግ ከጫፍ ደርሰዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በአስር ጨዋታዎች ተሰልፎ በድምሩ 380 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ ቀደም ብሎ ወልዋሎን ጨምሮ ከሌሎች ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቢቆይም መዳረሻው ስሑል ሽረ ለማድረግ
ተስማምቷል።

በታዳጊ ቡድን ደረጃ ለሐረር ዩናይትድ፣ለኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ እና ለመቻል ታዳጊ ቡድን መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ለመቻል፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጭምር መጫወት ችሏል።


በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በርከት ያሉ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ስሑል ሽረዎች የዊልያም ሰለሞን ዝውውር የመስኮቱ የመጨረሻው ዝውውራቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል።