አዳማ ከተማዎች የመሀል ተከላካይ አስፈረሙ

ላለፉት ዓመታት በንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ አዳማ ከተማ አቅንቷል።

በአሰልጣኝ አብዲ ቡሊ የሚመሩት እና በሊጉ ሁለት ጨዋታዎች አከናውነው በሦስት ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አዳማ ከተማዎች ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው የመሀል ተከላካዩ ፍቃዱ ደነቀን የግላቸው አድርገዋል።

እግርኳስን በአስኮ ፕሮጀክት ጀምሮ ከዛም በመቀጠል በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ንግድ ባንክ የታዳጊ ቡድኖች ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በክለብ ደረጃ ለመቐለ 70 እንደርታ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዋሎ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጫወት የቻለ ሲሆን ንግድ ባንክ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲመለስ አስተዋፆ ካደረጉ ተጫዋቾች ውስጥ ነው። አሁን ደግሞ ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ በኋላ መዳረሻውን አዳማ ከተማ ለማድረግ ፌርማውን አኑሯል።