ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ዝግጅት ጀምራለች

እየተካሄደ ባለው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በኋላ አሁጉራዊ ውድድሮችን ለማዘጋጀት እየሰራች እንደሆነ ተገልጿል።


የ16ኛው የኢትዮጵያ እግርኳስ የፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳረሽ መካሄድ ከጀመረ ሰዓታት ተቆጥረዋል በመድረኩ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት በተለያዮ ጉዳዮች ዙርያ ምላሽ እየሰጡ ይገኛል።

ፕሬዝደንቱ ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከል ኢትዮጵያ ከአራት ዓመት በኋላ በ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።

በ2029 ኢትዮጵያ አፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶበት አቅጣጫ ተቀምጦ እንቅስቃቄ መደረግ ጀምሯል ያሉት ፕሬዘዳንቱ በቅርቡም ሀገራችን የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በመዲናዋ አዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን አዘጋጅ ሀገር እንድትሆን የሚመጡ ተሳታፊዎችን ለማሳመን የቅስቀሳ ስራዎች እንደሚሰሩም ፕሬዝደንቱ አያይዘው ገልፀዋል።