ዋልያዎቹ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች በቴሌቪዥን ሽፋን ያገኛሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ እና ማክሰኞ ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኙ ታውቋል።


የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሦስት ቀናት ልዩነት ከጊኒ ጋር ላለበት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ከጀመረ ቀናቶች የተቆጠሩ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም መርሐ-ግብሮቹ ወደ ሚደረጉበት አይቮሪኮስት አቢጃን ጉዞውን አድርጓል።

በገለልተኛ ስታዲየም የሚደረጉት የኢትዮጵያ እና የጊኒ ጨዋታም በሀገራችን ብሔራዊ ጣቢያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ለአድማጭ ተመልካቾች እንደሚደርስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።