የኡመድ እና ሳላዲን ፍልሚያ በኡመድ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት በተደረገ ጨዋታ የኡመድ ኡኩሪ ክለብ የሆነው ኢትሃድ አሌሳሳድሪያ ባለሜዳውን የሳላዲን ሰኢድ ክለብ አል – አህሊን 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኡመድ ኡኩሪ የአሌሳንድሪያውን ክለብ ቀዳሚ ያደረገች ግብ ጨዋው በተጀመረ በ3ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የዛምቢያው ኢንተርናሽናል ፌሊክስ ካቶንጎ ላስቆጠረው ግብም አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

በጉዳት ለረጅም ጊዜያት በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ሳላዲን ሰኢድ ከእግር ጉዳቱ አገግሞ ተቀይሮ በገባበት ጨዋታ የአል – አህሊን ብቸኛ ግብ በ91ኛው ደቂቃ ላይ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሮ ወጥቷል፡፡

ከክለቡ ሊለቅ እንደሚችል ሲነገር የቆየው ኡመድ ባለፈው ሳምንትም ለኢትሃድ ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

የሀለቱ ኢትዮጵያውያን ግቦችን ይህንን ሊንክ ተጭነው መልከቱ

የኡመድ – https://m.youtube.com/watch?v=w5CwYrxagys

የሳላዲን – https://m.youtube.com/watch?v=U_9BcTdUYHY

ያጋሩ