ከፍተኛ ሊግ | ነቀምቴ ከተማ አዲስ አሰልጣኝን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆኑት ነቀምቴ ከተማዎች አዲስ አሰልጣኝ እና አስራ አምስት ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል።


በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ነቀምት ከተማ ለ2017 የውድድር ዘመን በአዲሱ ድልድል መሠረት በምድብ “ሀ” ስር የተደለደሉ ሲሆን ለውድድር ዘመኑንም ራሱን ለማጠናከር በዋና አሰልጣኝነት የቀድሞው ረዳቱን መሳይ አበበን በሀላፊነት የሾመ ሲሆን አስራ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም የስብስቡ አካል አድርጓል።

ክለቡን የተቀላቀሉት አዳዲስ ተጫዋቾች የቀድሞው የአዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ እና ሀምበሪቾ ተከላካይ ምንያምር ጴጥሮስ ፣ በሀላባ እና አርባምንጭ የተጫወተው አጥቂው አላዛር ዝናቡ ፣ በወልቂጤ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና የተጫወተው አማካዩ ቤዛ መድህን ፣ በአማካይ ቦታ ላይ በሲዳማ ቡና እና ወልድያ ተጫውቶ ወደ ቀደመ ቡድኑ የተመለሰው ሚካኤል ሀሲሳን ጨምሮ ታምራት በቀለ ተከላካይ ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ብሩክ ብርሀኑ አማካይ ከወልድያ ፣ ሀይሌ ጌታሁን አማካይ ከወልድያ ፣ ሀደሮ ሳሙኤል አጥቂ ከኦሮሚያ ፓሊስ ፣ አማኑኤል ጌታሁን አማካይ ከጅማ አባጅፋር ፣እሸቱ  ሀጪሶ ግብ ጠባቂ ከአዲስአበባ ፓሊስ ፣ ፂሆን ተስፋዬ ተከላካይ ከሲዳማ ቡና ፣ፋሲል ገረመው ተከላካይ ከሀዋሳ ከተማ ፣ ሰጠኝእየሱስ ታረቀኝ ተከላካይ ከአቃቂ ፣ ሔኖክ ሂርፓቶ ግብ ጠባቂ ከኮልፌ እና ተካልኝ መስፍን አማካይ ከደሴ ከተማ ለቡድኑ የፈረሙ አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ሆነዋል።