ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ከሰዓታት በኋላ የሚደረግ ጨዋታን ይመራሉ

አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ የማርያ መርሃግብርን ዛሬ ይዳኛሉ።

በ2025 ለሚሰናዳው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣሪያ ጨዋታዎችን የተለያዩ የአህጉሪቱ ሀገራት እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን በምድብ 11 በዛሬው ዕለት የሚከናወን አንድ ጨዋታን አራት ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች በጣምራ እንዲመሩት ተመድበዋል ፤ ከሰዓታት በኋላ አስር ሰዓት ሲል በምድቡ ግርጌ ላይ ያለምንም ነጥብ የተቀመጠችው ማላዊ በሜዳዋ ከቡሩኪናፋሶ በመቀጠል በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ በሰባት ነጥብ ከተቀመጠችው ቱኒዚያ ጋር በቤንጉ ስታዲየም መርሃግብራቸውን ይከውናሉ።
ይህንን ጨዋታ ደግሞ በመሐል ዳኝነት በአምላክ ተሠማ ሲመራው ረዳቶቹ በመሆን ከቀናቶች በፊት በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ተሳትፎ የነበረው ትግል ግዛው እና ፋሲካ የኋላሸት ሲሳተፉ በላይ ታደሠ በአንፃሩ አራተኛ ዳኛ ሆኖ የሚመሩት ይሆናል።