“ ሦስት ፣ አራት ክለቦች የክፍያ ስርዓት መርያውን ለመጣስ ሲሞክሩ አግኝተናል”- መቶ ዓለቃ ፈቃደ ማሞ

የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር በአዲሱ የክፍያ ስርዓት አፈፃፀም ሂደት ዙርያ በፕሬዝደንቱ አማካኝነት ለጋዜጠኞች ምላሽ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር 6ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል መካሄዱ ተከትሎ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት በቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይናስቲ ሆቴል እየሰጡ ይገኛል።

እየተሰጠ ባለው  ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሚዲያ አካላት ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የአዲስ በወጣው የክፍያ ስነ ሥርዓት አፈፃፀሙ እንዴት አገኛቹሁት ? የምትፈልጉትን ቁጥጥር አድርጋቸዋል ወይ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ቅሬታዎች በተወሰኑ ክለቦች እየተነሳ ይገኛል በሚል ለተነሳው ጥያቄ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ምላሽ ሲሰጡ
“ በጉባኤው ላይ ከተነሱ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች  መካከል አንዱ የክፍያ ሥርዓቱ አፈፃፀም በተመለከተ ነበር። በዚህ የክፍያ ስነ ሥርዓት መመርያ ዙርያ ሁለት አንኳር ጥያቄዎች ተነስተዋል።” ያሉት መቶ ዓለቃ ፈቃደ “አንደኛው እኛ በቅንነት ብዙ መረጃ ሠጥተን ነገር ግን ተግባራዊ ባለመደረጉ ክለባችን ተጎድቷል። በዚህም የ2017 ውድድር መውረድም፣ ሻምፒዮን የሚሆን ክለብ መኖር የለበትም።” የሚል ሲሆን “ሁለተኛ ደግሞ በቅንነት  ያቀረብነው የተጫዋቾች ደሞዝ የተጣራው እንዲቀርብ ፈልገን የነበረ ቢሆንም ያልተጣራ መቅረቡ ተገቢ አይደለም።”የሚል ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ገለፀዋል።

ማብሪራያቸውን ሲቀጥሉ ይህን የፋይናስ ስርዓት ዝም ብለን ያወጡት አለመሆኑ እና ጥናት ተደርጎበት እንደሆነ ያብራሩት ፕሬዝደንቱ ብዙ ክለቦች ተግባራዊ ለማድረግ ሲፎካክሩ ቢቆዩም ሐምሌ ወር ሲመጣ ግን አብዛኛዎቹ ባይባልም ሦስት አራት ክለቦች የክፍያ ሥርዓቱ ጥሰው አግኝተናል ብለዋል።
መመርያውን ጣሱ ስለተባሉ ክለቦች ሲያስረዱም “ለምን እነዚህ ክለቦች ህጉን ጣሱ ቢባል ለኪሳቸው አስበው መመርያውን የጣሱ አሉ ይሄን ለመናገር አልፈራም በግልፅ ነው የምናገረው። ለምሳሌ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወት የነበረ አንድ የውጭ ሀገር ተጫዋች ሦስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ያገኝ የነበረ ተጫዋች መቻል ሲገባ መቶ ሺህ ብር መከፈሉ በግልፅ መመርያው መጣሱን ማሳያ ነው። ሌሎች ብዙ መረጃዎች ይዘናል። የቀድሞ ክለባቸው የሚሰጣቸውን ከፍተኛ ብር አንቀበልም ብለው በአነስተኛ ክፍያ ሌላ ክለብ የሄዱ አሉ ። በአጠቃላይ መረጃዎች እየተሰባሰቡ እየተጠናከሩ ይገኛል። የተዋቀረው ኮሚቴ ጉዳዮን እየመረመረ ነው በጊዜ ሂደት መፍትሄ ያገኛል። ምንም በማያወላውል ሁኔታ እርምጃ እንወስዳለን የጊዜ ሁኔታ ነው። ይህን ላረጋግጥላቹ እፈልጋለው።” ብለዋል።

በመጨረሻም በክረምቱ ከተረደጉ ዝውውሮች ውስጥ 25 ተጫዋቾች ጥርጣሬ ውስጥ ገብተው ስማቸው እና ማስረጃዎችን አጠናክሮ ለመርመር ለኮሚቴው ስማቸው ስለመተላለፉ አንስተዋል።