👉የወልቂጤ ከተማ ጉዳይ እኛን የሚመለከት አይደለም…”- የሊጉ አክስዮን ማህበር ፕሬዝደንት መቶ ዓለቃ ፈቃደ ማሞ
በቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይናስቲ ሆቴል የሊጉ አክሲዮን ማህበር ሰሞኑን በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ዙርያ ጋዜጣዊ እየሰጡ ይገኛል ፤ፐከሚዲያ አካላት ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የወልቂጤ ከተማ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምንድነው? በአክስዮን ማህበሩ አባልነት ይቀጥላል ወይስ በሚል ለተነሳው ጥያቄ የአክስዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ ዓለቃ ፍቃደ ማሞ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
“ የወልቂጤ ከተማ ጉዳይ እኛን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም። ግን ምን ሆነ መሰላቹ ወልቂጤ ከዚህ ቀደም ይጫወቱ ለነበሩት ተጫዋቾቹ ክፍያ መፈፀም አልቻለም በዚህም ተጫዋቾቹ ክስ አቅረበው ነበር። ፌዴሬሽኑም ለተጫዋቾቹ ክፍያ እንዲፈፀም ባለመድረጉ ሃምሳ ሺህ ዶላር ተቀጥቶ ነበር። መነሻው ይሄ ነው። ከዚህ በመነሳት ፌዴሬሽኑ ወልቂጤ ከተማን ካልከፈላቹሁ አገልግሎት አንሰጣችሁም ተባሉ። ተጫዋችን ማዘዋወር አትችሉም ተባሉ ፤ እኛ ውድድር ስንጀምር መርሃግብር ሲወጣ እንደ ተወዳዳሪ ክለብ አቅርበነው ነበር። ሆኖም ውድድሩ ሲጀምር ይዞ የመጣው ሁለት ሦስት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው ቲሴራ ያላቸው ይህን ሳያሟሉ ሁለት ጊዜ ፎርፌ ሰጡ በእኛ የውድድር መመርያ ደንብ መሠረት ደግሞ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ ፎርፌ የሰጠ ቡድን ከውድድር ይሰናበታል። በዚህ መሰረት ተሰናብቷል ይግባኝ ጠይቋል እንደሰማቹሁት ይግባኙ ስርዓቱን ያልተከተለ ነበር በሚል ውድቅ ተደርጎበታል። ስለዚህ የፍትህ አካላት በወሰኑት ውሳኔ እኛ ጣልቃ አንገባም ያለቀለት ጉዳይ ነው። “በማለት መቶ ዓለቃ ፈቃደ ምላሽ ሰጥተዋል።
በማስከተል በአክስዮን ማህበር አባልነቱ ይቀጥላል ወይ በሚለው ዙርያ አቶ ክፍሌ ሰይፉ ሲመልሱ “ከአክስዮኑ አባልነቱ ጋር በተያየዘ ጉዳዩ በይግባኝ ስላለ በማህበር አባልነቱ ይቀጥላል የሚለው በአክሲዮን ማህበራችን አባልነቱ በአንዴ ውጣ አይባልም። በጊዜ ሂደት አካሄዱን መሰረት ተደርጎ የሚወሰን ይሆናል ።”ሲሉም ተደምጠዋል።