መቶ ዓለቃ ፈቃደ ማሞ ስለትግራይ ክልል ክለቦች ምን አሉ?

ሦስቱም የትግራይ ክለቦች ከምስል መብት ጋር በተያያዘ እና የአክሲዮን ማህበሩ አባል በመሆን ከፋይናሱ ገቢ ተጠቃሚ በሚሆኑበት ዙርያ ላነሱት ጥያቄ መቶ ዓለቃ ፍቃደ ማሞ ተከታዮን ምላሽ ሰጥተዋል

“በ2015 የትግራይ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ይሳተፉ በሚል ለውይይት ተጠርተን ነበር፤ በኛ በኩል እንደ ድሮ ክለቦች በዘፈቀደ የሚገቡበትና የሚወጡበት አይደለም። ‘ሼር ካምፓኒ’ ነው ግዴታ አለበት ከዓለማቀፍ ድርጅት ጋር ውል ተዋውለናል ስለዚህ በዚህ ጉዳይ የትግራይ ክለቦች አባል ሳይሆኑ እንደ አባል ቆጥረን ልናስገባ ልናወዳድር አንችልም የሚል ነበር የኛ አቋም። 2015 በዚህ ታለፈና 2016 በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ክለቦቹ ባሉበት ይመለሱ የሚል ውሳኔ ከመንግስት መጣ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም ሰፊ ውይይት አድርገናል። የሚመለሱ ከሆነ መንግስት የሼር ካምፓኒ ላይ እገሌ ይግባ እገሌ ይውጣ ብሎ የመወሰን ስልጣን የለውም እንደማንኛውም የንግድ ድርጅት የተቋቋምን ነን ስለሆነም ሼር ካምፓኒው ውስጥ ገብቶ አበበን ተቀበል አልማዝ ተቀበል የሚል የኢትዮጵያ ህግ አይፈቅድም፤ ስለሆነ የምንቀበልበት መንገድ የለም ነው። ”
“ይሄ የሚመነጨው ከብሮድካስትም ከምንም ጉዳይ ጋር አይደለም፤ ከሼር ካምፓኒው አባልነት ነው። እርግጥ ነው ውድድር ይካሄዳል እንደሚታወቀው እንደድሮ አይደለም። በዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክለቦችን በመቐለ 70 እንደርታ አማካኝነት ባለፈው ጉባኤ ላይ ወንድሞቻቹህ ነን እና በዚህ ጉዳት ላይ አስተያየት አድርጉልን የሚል ለጠቅላላ ጉባኤው ጥያቄ አቅርበዋል፤ የመብት ጥያቄ ሳይሆን የሞራል ጥያቄ ነው የቀረበው።”