የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን በታንዛኒያ የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ስለውጤት መጥፋቱ ያላቸውን ሀሳብ ተናግረዋል።
በአሰልጣኝ ሥዩም እየተመራ በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ታንዛኒያ በማቅናት በሦስቱ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዶ በጊዜ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውድድር ላይ የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል። ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም ፤
“ከምልመላ አንስቶ እስከ ዝግጅት ድረስ እጅግ የተጨናነቀ ቀን ነበረን። ምንም ይሁን ምን በውጤቱ ሰፊውን የስፖርት ቤተሰብ ይቅርታ እጠይቃለው፤ መተራረም የሚቻለው ከዚህ ቀናነት የሚጀምር ስለሆነ ነው። በውጤት በኩል የጠበቅኩት ነገር ባይመዘገብም የቡድኑ እንቅስቃሴ አንገት የሚያስደፋ አልነበረም። ጥሩ ጊዜን አሳልፈን መጥተናል።”ብለዋል።
አሰልጣኝ ሥዩም ካላቸው ሰፊ ልምድ ይሄን ኃላፊነት መረከብን እንዴት ያዩታል ተብለው ሲጠየቁ “ኃላፊነቱን ስረከብ ካለኝ ልምድ በመነሳት ከታች ላሉት ወጣት አሰልጣኞች እንዳግዝ ተደርጌ አምኜበት የወሰድኩት ኃላፊነት ነው። በሀገራችን ውስጥ ካሉ ትልልቅ አሰልጣኞች አንድ ብትመርጡ እኔ ነኝ ሁለትም ብትመርጡ እኔነኝ።”በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ሌሎች የሰጧቸውን ተያያዥ መረጃዎችን ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለስበታለን።