የካፍ ሴቶች ቻምፕዮንስ ሊግ ውድድር በሞሮኮ ይካሄዳል

ሴካፋ ዞን ሻምፕዮኖቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የሚሳተፉበት ውድድር በሞሮኮ እንደሚዘጋጅ ታውቋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ ኣካል የሆነው ካፍ ሞሮኮ የ2024 የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ  ውድድር እንደምታዘጋጅ ይፋ አድርጓል ፤
ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 14  በሞሮኮ አዘጋጅነት እንዲካሄድ መርሃግብር በወጣለት ውድድር የሴካፋ ሻምፕዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨምሮ የወቅቱ የውድድሩ ሻምፕዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ቲፒ ማዜምቤ፣ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ፣ ኤግልስ ዴ ላ መዲና፣ ኤዶ ኲዊንስ፣ ቱታንካሙን እና ‘AS FAR’ የሚሳተፉበት ሲሆን አሸናፊውም 400,000 ዶላር እንደሚያገኝ ይፋ ሆኗል።
በውድድሩም ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በሁለት አጋጣሚዎች ውድድሩን ያሸነፉት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና የአዘጋጅዋ አገር ክለብ የሆኑትና ከዚ ቀደም ውድድሩን ያሸነፉት ‘ASFAR’ ውድድሩን ለማሸነፍ ቅድመ ግምት ያገኙ ክለቦች ሆነዋል።