👉 “ጊኒ በከፍተኛ ሁኔታ ይበልጠናል። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ማመን ያስፈልጋል…
👉 “ገና ለገና እንደዚህ ይሆናል ብዬ መተንበይ አልፈልግም…
👉 “የተጋነነ ነገር ያለ አድርጋችሁ አትውሰዱት..
ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንደማይቆዮ በግልፅ ያሳወቁት አሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በመጨረሻም ከመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች የተለያዮ ጥያቄዎች ተነስተውባቸው የሰጡትን የመጨረሻ ምላሽ በተከታይነት አቅርበነዋል።
የአካል ብቃት ፣የስነ ልቦና እና የቪዲዮ አናሊስት ባለሙያዎችን ከመጨመር ጋር ተያይዞ ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ቅጥር እንዲፈፀምሎት ለምን አልጠየቁም ?
”ፍጥነት በነገራችን ላይ በዚህ ጊዜ አይመጣም። ፍጥነት የአካል ብቃት አሰልጣኝ ስለቀጠርን አይመጣም። ሌላ የአካል ብቃት ስራዎች ሊመጡ ሚችሉ ነገሮች አሉ። እውነት ለመናገር ፍጥነት በዚህ ዕድሜ ሊመጣም ፤ ልሻሻልም አይችልም። ሌላውን ግን የሺዲዮም ይሁን አይተናል። የቪዲዮ አናሊስት ባለመኖሩ የተፈጠረ ችግር ሳይሆን ልዩነታችን ነው ያመጣው ነው። በጣም ግልፅ ነው የነበረው ልዩነት በተለይ በተለይ ከዚህ ከመሃል እስከ አጥቂ ያለው የጊኒ ተጫዋች ጠንካካራ ቡድን ነው። አንድ ቡድን ነው የገጠምነው ሚታውቁት ነው። ሁለት ሶስት ቡድን አይደለም የገጠምነው። ከዛ በፊት ከነበረው የታንዛኒያ እና ከኮንጎ ጨዋታ ጊኒ በጣም በብዙ ነገር የተሻለ ነው። ስለዚህ የተጋነነ ነገር ያለ አድርጋችሁ አትውሰዱት። የዓለም መጨረሻ ወይንም ፍፃሜ አይደለም። ገብቶብናል እናውቃለን። ሽንፈት አጋጥሞናል። ነገር ግን በማነው የተሸነፍነው እኛ የምናሰልጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር ነው የተጫወትነው ሌላ ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም የገጠምነው። ጊኒ በከፍተኛ ሁኔታ ይበልጠናል። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ማመን ያስፈልጋል። ይሄ ሀገራችን ከዚህ ቀደም የምታረጋቸውን ጨዋታዎች ከአስሩ ጨዋታ አንድንም ጨዋታ በሜዳችን አላደረግንም የሚታወቅ ነው። ግን በሜዳ መጫወት ምን ያህል አድቫንቴጅ እንዳለው ሁለቹም ሚታውቁት ነው ከእናንተ ሚሰወር አይደለም። ጊኒን በገጠምነው በሁለቱም ጨዋታ ባለሜዳ የሚመስሉት እነርሱ ነበር። ሙሉ ስታዲየሙ ደጋፊ ነበር። ባለሜዳ ስትሆን ብዙ ነገሮች አድቫንቴጅ ትውስዳለህ። የአልቲቲዩድ የኛ ከሌሎች የተለየ ነው። በተለይ አልቲቲዩድ ጠቀሜታ አለው አንዱ እሱ ነው። ሁለተኛ የዳኛ ተፅዕኖ አለ አንዳንድ በተፅእኖ ሚወስኑ ውሳኔዎች ነበሩ። ስለዚህ እርግጠኛ ሆኜ ነው ምነግራችሁ እኔ አሁን እንደነገርኳችሁ ነው ለቀጣይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው እንዲጫወት ጥረት ማድረግ አለባችሁ። መወትወት አለባችሁ። ሁላችንም የድርሻችንን መውጣት ያለብን ይመስለኛል። ይሄ ካልሆነ ግን አስቸጋሪ ነው አሁንም ሊቀጥል ይችላል። ገና ለገና እንደዚህ ይሆናል ብዬ መተንበይ አልፈልግም ግን በጣም ከባድ ነው። ሜዳችን ላይ የምናገኛቸው ውጤቶች ለቀጣይም ጨዋታዎች ተፅዕኖ ይፈጥራሉ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ስለዚህ በሜዳችን በማንጫወትበት ሰዓት ላይ እንደዚህ ተመዝኖ አስቸገሪ ስለሚሆን ማለት ነው። የምንጫወት የምንገጥማቸው ቡድኖች በጣም ከፍተኛ የሆነ ደረጃ ላይ ያሉት ናቸው እስከአሁን የገጠምናቸው ማለት ነው።
ባለፉት ጨዋታዎች ብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጎል ገብቶበት ሽንፈት አስተናግዷልና አጨዋወተን ይዤ ቀጥላለው ካሉ የቱ ጋር ነው ክፍተቶች ያሉት?
”ጎሉ ልገባ የሚችለው አንዱ ልዩነት እንዳለ ነው፣ ሁለተኛ አድቫንቴጅም ምንወስዳባቸው ነገሮች አሉ።በሜዳችን እራሱ አይደለም ኮንጎ ጊኒ ቢሳኦውን አይታቿ እንደሆነ በሜዳቸው ነው አቻ የወጣነው ቻሌንጅ አድርገን ማለት ነው።እዚህ ቢመጣ ዲሞክራትክ ኮንጎን በእርግጠኝነት ምላችሁ ኢትዮጵያ ያሸንፋል ምንም ጥርጥር የለውም በብዙ ነገር ማለት ነው። ሴራሊዮንም ቢታዩ እዚህ ቢመጣ ምን ያህል ተከናንቦ እንደሚሄድ ግልፅ ነው። ስለዚህ ጊኒም ቢመጣ እዚው ይሸነፋል። እዛ ሊያሸንፈን ይችላል ግን እዚህ ይሸነፋል። አድቫንቴጁ ምን ያህል ልዩነት እንዳለው ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛ አጠቃላይ የስነልቦና ጉዳይም ለውጥ እያመጣ ነው። በሜዳህ እየተጫወትክ አንዴ ሊታሸንፍ አንዴ ሊትሸነፍ ትችላለህ ያ ግን በተጫዋቾችም በአጠቃላይ በህዝባችንም በሁላችንም ዘንድ ሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀለል ያለ ነወ። እንደ አሁኑ ከባድ አይሆንም። አሁን ሁሉንም ጨዋታ እዛ ሲናረግ ግን የምያጋጥመን ይሄው ነው።ስለዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ስለነበር ነው።”
የቪዲዮ አናሊስት እና የስነ ልቦና ባለሙያዎች አያስፈልጉም አቅም የለንም በሚል ለሰጡት አስተያየት ሲመልሱ
”አያስፈልግም ከነጭራሹ የምል ምላሽ አልሰጠውም።ግን ሁኔታዎች አልተመቻቹም ነበር በወቅቱ ከግዜ አንፃር በሚለው ማለት ነው። ከዛ በኋላ ደግሞ ሰው ለማግኘት ጥረት ምናደርግበት ግዜ አንዱን ቪዲዮ አናሊስት ስንፈልግ ሌላ ነገር ይኖራል። እንደዚህ አይነት ነገሮች አሉና ከዚህ የነበሩ ልጆች ወደ ውጪ ሄደው ነበር። እንደዚህ የተለያዩ ምክንያቶች ነበሩና ይሄ ካልሆነ በስተቀረ ባለሙያዎች አያስፈልጉም የሚል ጭራሽ አራት ነጥብ የተደረገበት ነገር የለም።”
የጊኒው አጥቂ ተፀዕኖ ፈጣሪ ተጫዋች መሆኑን ካወቃችሁ ለምን ተጫዋቹ ላይ ትኩረት ያደረግ መከላከል መንገድ ይዛችሁ አልገባችሁም?
”የተጋጣሚን ሁኔታ አውቆ መዘጋጀት ነበረብን እሱ ልክ ነው። አንዱ የተዘናጋንበት እሱ ነው። አንዱ ስህተቱ ያ ነው። ስህተት ውስጥ ያስገባን ያልነበሩ ተጫዋቾች ናቸው እነዚህ እነሱን ማነጅ ማድረግ አልቻልንም። ግን ከተጫወትን በኋላ እሱ ላይ ትኩረት እንድናደርግ ማርክ እንዲያደርጉ ጥረት አድርገናል። ቀድመንም ይሄን የቤት ስራ ሰጥተን ነበር። አንድ ክፍተት ሲያገኝ ጎል አግብቷል ተጫዋቹ ያው በጣም ልምድ ያለው ነው። የሀገርቱ የጀርመን ኮከብ ጎል አግቢ ነው። አሁንም በቅርብ እንኳን ቻምፒየንስ ሊግ ጋርም ስድስት ጎል አግብቷል።እኛ ላይ አምስት ጎል አግብቷል። ይሄ ልዩነት ፈጣሪ እንደሆነ በግልፅ የታየ ስለሆነ ምንም መደበቅ አይቻልም።
የአቀም ልዩነት አለ ሚባል ነገር አሳማኝ አይደለም ይሄን እንዴት ይገልፁታል?
”ጊኒ ባለው ደረጃ አሁን ደግሞ ቢታይ በጣም ጥሩ ነው። ስለዚህ ልዩነት ባለበት ሰዓት ልዩነት አለ ብሎ ማመን አስፈላጊ ነው። አይሸነፍም ማለት አይደለም ግን ልዩነት እንዳለበት መታወቅ አለበት።”
በሜዳችን ብንጫወት ኖሮ ለሚለው ጥያቄ ከዚህ በፊትም በሜዳችን በሌሰቶ ጨዋታም አይተናልና በጥልቀት አይታቹታል ወይ?
”በሜዳችን አናሸንፍም የሚል አቋም ካላችሁ ያ የራሳችሁ እምነት ነው።እዚህ በሜዳችን አንድ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር አሸነፍን ተሸነፍን።ግን በተደጋጋሚ ከሱዳን ጋር አሸንፈናል አይደለ ለምን አላነሳችሁትም? ከዛስ በኋላ ሌላ ጨዋታ ዩጋንዳን በሻዶው ቡድንም ቢሆን አሸንፈናል። ከዛ በላይ ደግሞ ትልልቆች ቡድኖች መጥተውም ብንጫወት በጣም የተሻለ ነው የማሸነፍ እድሎችም ይኖራሉ። የወዳጅነት ጨዋታም እያደረግን ብንሄድ በጣም የተሻለ ነገር እናገኝበታለን ብለን እናስባለን። ሜዳ ላይ የመጫወት ጥቅሙ ምንም ጥርጣሬ የለውም። ሜዳ ላይ መጫወት መቶ ፐርሰንት ባይሆንም ሰማንያ ፐረሰንት እድል ስላለው ማለት ነው። ስለዚህ ይሄ በሜዳችን ስላልተጫወትን ነው እየተሸነፍን ያለነው የሚለው ያለው ኢምፓክት ትልቅ ነው ለማለት ነው።