በምሽቱ መርሐግብር ምዓም አናብስት እና መቻሎች አቻ ከተለያዩ በኋላ የሁለቱም ክለቦች አሰልጣኞች ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐየ – መቐለ 70 እንደርታ
”ሁለት ሦስት ማግባት የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም እንጂ በመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታውን መጨረስ የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ ያንን ማድረግ ስላልቻልን በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው ጠንከር ሊል ችሏል።”
አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል
”ጨዋታ አቋርጠህ ስትመጣ የተጫዋቾች ኢንተንሲቲ ይቀንሳል፣ እስኪዋሃዱ ድረስ እንጂ በፍፁም ቡድናችን ጥሩ ነው። የምንጫወተው ጨዋታም ጥሩ ነው በግንቦት ወር አካባቢ ተገቢው ቦታ ላይ እንገኛለን።”