ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ ከአዳማ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
“ውድድሩ ተቋርጦ ከመጀመሩ አንጻር በእንቅስቃሴ መጥፎ አልነበርንም። ተጋጣሚ ቡድን ወደ ራሱ ሜዳ ወርዶ መጫወቱ ደግሞ ትንሽ አክብዶብናል ፤ በቀይ ካርድ ሰው ማጣታቸውም ተነሳሽነታቸውን ጨምሮታል። አድቫንቴጅ ቢኖረውም የቁጥር ብልጫ ብቻውን እንድታሸንፍ አያደርግም ፤ ጉጉት እና ስሜታዊነት ታይቶብናል።”
አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ
“ከቀይ ካርዱ በፊት ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እያደረግን ነበር ካርዱ ረብሾናል። ተጫዋቹ አውቆ እንዳልተማታ ነው የማስበው። በውጤቱ ደስተኛ ነኝ። ቢኒያም ዐይተን ብዙ ስቴፕ መሄድ የሚችል ተጫዋች ነው ብዙ ይቀረዋል።”