በዕለቱ ቀዳሚ በነበረው መርሃግብር ኢትዮ ኤሌክትሪኮች የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ድላቸውን ካሳኩበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
“በጠንካራው ጨዋታ ድል ማድረጋችን የማሸነፍ ስነልቦናችንን ከፍ ያደርጋል ፤ በውጤቱ ኮርቻለሁ በልጆቼም በጣም ደስተኛ ብሆንም ከዚህ በላይ ማድረግ እንደሚችሉ አምናለሁ።”
ደግአረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ
“በዛሬውን ጨዋታ ቡድናችን ያደረግው እንቅስቃሴ በጠበቅነው ልክ አላገኘነውም ፤ እንደ ቡድን ወርደን ነው የቀረብነው።”