የጨዋታ ሳምንቱ ማሳረጊያ በነበረው መርሃግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድንን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
ዘላለም ሽፈራው – ሲዳማ ቡና
“የሀዋሳ ከተማው ሽንፈት ቁጭት ፈጥሮብን ነበር ፤ በዛሬው ጨዋታ ከፍተኛ ጥድፊያ ውስጥ ነበርን ፍፁም ተረጋግተን ለመጫወት አልቻልንም።”
ገብረመድህን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን
“ግብ ከተቆጠረ በኋላ መፍጨርጨር ትርጉም የለውም ፤ ከመጀመሪያው ትኩረት አድርገን መጫወት ይገባናል።”