በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ መትረፉን ያረጋገጠው ስልጤ ወራቤ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ዘለግ ያለ የውድድር ተሳትፎን ካደረጉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ስልጤ ወራቤ የተጠናቀቀውን ዓመት በመጨረሻ የሊግ ጨዋታውን ለከርሞው በሊጉ ላይ መቆየቱን ማረጋገጡ ይታወሳል።
ለያዝነው የ2017 የውድድር ጉዞው ባሳለፍነው ዓመት አጋማሽ በአሰልጣኝነት ተረክበውት በነበሩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ በርካታ ተጫዋቾች ውል ያላቸው በመሆኑ በጥቂት ዝውውሮች ላይ ብቻ በመሳተፍ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል።
የቀድሞው የለገጣፎ ለገዳዲ እና የአምናው የሸገር ከተማ ግብ ጠባቂ ሚኪያስ ዶጂን ፣ በቤንች ማጂ ቡና ፣ አርባምንጭ ከተማ እና በክረምቱ ወደ ወልቂጤ አምርቶ የነበረው አጥቂው ወንድማገኝ ኪራን ጨምሮ ሲሳይ ጥበቡ ተከላካይ ከሸገር ከተማ ፣ ጌታቸው ተፈራ አማካይ ከጅማ አባጅፋር ፣ ሊዮናርዶ ሠለሞን አማካይ ከወልድያ እና ቢኒያም ፀጋዬ ተከላካይ ከአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ አዲሶቹ ፈራሚዎች ሲሆን የግብ ጠባቂው ፍቅሩ ወዴሳ ፣ የተከላካዩ አማኑኤል ተስፋዬ እና የአጥቂው ስዩም ደስታ ኮንትራት ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት አድሰዋል።