ጊዜያዊው የዋልያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ለሚያከናውናቸው የቻን ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፈዋል።
ግብ ጠባቂዎች
ሰዒድ ሀብታሙ – ሀዋሳ ከተማ
በረከት አማረ – ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
ዳግም ተፈራ – አዳማ ከተማ
ተከላካዮች
አሥራት ቱንጆ – ድሬዳዋ ከተማ
ያሬድ ባየህ – ሲዳማ ቡና
ደስታ ደሙ – ሲዳማ ቡና
ሱሌይማን ሀሚድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍሬዘር ካሳ – ባሕር ዳር ከተማ
ረመዳን የሱፍ – ኢትዮጵያ መድን
ወልደአማኑኤል ጌቱ – ኢትዮጵያ ቡና
ራምኬል ጀምስ – ኢትዮጵያ ቡና
አማካዮች
ጋቶች ፓኖም – ኢትዮጵያ መድን
በረከት ወልዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አብዱልከሪም ወርቁ – መቻል
አብነት ደምሴ – ወላይታ ድቻ
እንዳልካቸው መስፍን – አርባምንጭ ከተማ
ቢኒያም ዐይተን – አዳማ ከተማ
አጥቂዎች
መሐመድኑር ናስር – ድሬዳዋ ከተማ
ኪቲካ ጅማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፋሲል አስማማው – ስሑል ሽረ
በረከት ደስታ – መቻል
አማኑኤል ኤርቦ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቸርነት ጉግሳ – ባሕር ዳር ከተማ
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ ጥቅምት 14 ከ7 ሰዓት ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩም ጥሪ ቀርቧል።