የ2017 የሴቶች ሊጎች የት ይደረጋሉ?

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚደረጉት ሁለቱ የዕንስቶቹ ውድድሮች የሚደረጉባቸው ከተሞች ተለይተዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በዛሬ ዕለት ከረፋድ ጀምሮ በአዲስ አበባ ካሌብ ሆቴል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች የክለብ ኃላፊዎች እና ተወካዮች በተገኙበት እየተደረገ ይገኛል። ጥቅምት 24 እንደሚጀመሩ ቀደም ተብሎ በውድድር ዳይሬክቶሬት በኩል ይፋ የተደረጉት እነዚህ ውድድሮች በሁለት ከተሞች እንደሚደረጉ በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ዙር ውድድር አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሲከናወን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የመጀመርያው ዙር ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ላይ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር

ቦሌ ክ/ከተማ ከ አዳማ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መቻል
ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ
ባህር ዳር ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ከ ልደታ ክ/ከተማ
ሀምበርቾ ከ አርባምንጭ ከተማ

የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የመጀመርያ ሳምንት መርሐ ግብር

ሸገር ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ
ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
ኡራ አፋፍሪ ከ ይርጋጨፌ ቡና
ጥሩነሽ ዲባባ ስ/አ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፋሲል ከነማ ከ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ ወላይታ ድቻ