ምዓም አናብስት ብርቱካናማዎቹን ካሸነፉበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱም ክለብ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ
”መጠቀም አለመቻላችን ነው እንጂ ከእረፍት በፊት ያገኘናቸውን ኳሶች ብናስቆጥር ኖሮ ጨዋታው ያን ጊዜ ያልቅ ነበር። ደጋፊያቸው ውስጥ ሆኖ ካለው ጫና ሁኔታዎች ያንን ሦስት ነጥብ ይዘን መውጣታችን ለቀጣይ አንድ ስቴፕ እያሳዩ የሚሄዱ ነገሮች አሉ።”
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – ድሬዳዋ ከተማ
”ጨዋታ ጥሩ ነበር አይባልም መቼስ ተሸንፈህ። እጃችን ላይ የያዝነውን ነጥብ ነው የጣልነው ፤ በካውንተር አግኝተውናል። ቀጣይ ጨዋታዎች ብሩህ ይሆናሉ። የተሻለ ጨዋታ ለተመልካች ያሳያሉ ፤ የተሻለ ነጥቦችን እንይዛለን።”