የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ፋሲል ከተማ ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ክለብ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን ብለዋል።
አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
”ከፈጠርናቸው የግብ እድሎች አንፃር አጨራረስ ላይ ድክመት ነበረብን። እንደተጀመረ አካባቢ ያገኘናቸውን እድሎች ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ ከዚህ የተሻለ ነጥብ እናስመዘግብ ነበር። የገጠምነው ቡድን ጠንካራ እና ትልቅ ነው ከዚህ አንፃር መጥፎ ውጤት አይደለም።”
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
”ከሌሎች ጨዋታው የዛሬው ይሻላል። ይሄን ጨዋታ የተጫወትነው ሰባ ሁለት ሰዓት ሳይሞላ ነው ስለዚህ ከፕሮግራም አወጣጥ ጀምሮ ትክክል አይደለም። የምታገኘው ቡድን ተመሳሳይ ቀን አርፎ የሚመጣ አይደለም።”