አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።
አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ
”የበለጠ ጎል ማስቆጠር ምንችልባቸውን አጋጣሚዎችን ፈጥረናል።በድናችን ከዕለት ዕለት ጥሩ እየሆነ ነው።በአሁን ሰዓት ስለችግር አናወራም ስለቡድን ግንባታ ብቻ ነው ምናስበው።”
አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ
”አጥቂዎቼ እንደበፊቱ የሚገኙትን ኳስ ያለመጠቀም ችግር ዛሬ ጎልቶ ነው የታየው።የሚሳቱ ኳሶች ዋጋ አስከፍለውናል።ተከላካይ መስመራችን አሁንም ማረም ያስፈልገዋል።የውጪ ዜጎችን ለማምጣት በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርጌያለሁ።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link