በቻን ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋር የተደለደለችው ኤርትራ ጨዋታዎቹን እንደማታከናውን አሳውቃለች።
በምስራቅ አፍሪካ ሦስት ሀገራት በሚዘጋጀው የ2025 የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ በየቀጠናው የማጣሪያ መርሐ-ግብሮች ቀጠሮ የተያዘላቸው ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ከጎረቤት ሀገር ኤርትራ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ለማድረግ ዝግጅት ጀምራለች።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም እንደሚደረጉ በሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መግባባት ላይ ተደርሶ የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት በተሰማ መረጃ ኤርትራ ከማጣሪያው ጨዋታ ራሷን ማግለሏ ታውቋል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወጣለት መርሐ-ግብር ከታንዛኒያ አቻው ጋር ቀጣይ መርሐ-ግብሩን የሚከውን ይሆናል።