የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ኢትዮጵያ መድን

ሁለቱን የመዲናችን አዲስ አበባ ክለቦችን ያገናኘው ጨዋታ ያለግብ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

”ጨዋታው ከባድ ነው መድን ካለው አቅም አንጻር። አንድ ነጥብ ማግኘታችን ባንፈልገውም መጥፎ አይደለም። ያሰብነውን አድርገናል ግን ከአጥቂዎቻችን ጋር የነበረው ግንኙነት ጥሩ ስላልነበረ የምንፈልገውን ነገር አላገኘንም።”

አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን

”በጣም ብዙ ወደ ጎል ቀርበናል ፤ ብዙ ስተናል አሁን ብዙ ጎል ያስፈልገናል። አንድ ጊዜ ሲከፈትልህ የግድ ይከፈታል። ጎል አካባቢ የመረጋጋት ነገር አይታይም። ወደ ሪትም ለመመለሰ ወሳኝ ጨካኝ የሆነ አጥቂ ያስፈልጋል።”

ሙሉውን ለማድመጥ ተከታዩን ይጫኑ 👉 LINK