ከፍተኛ ሊግ | የካ ክፍለ ከተማ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚወዳደረው የካ ክፍለ ከተማ የአስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲቋጭ የአስራ አንድ ነባሮችን ኮንትራትም አድሷል።

በአሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸው ላለፉት ተከታታይ ዓመታት እየተመራ በከፍተኛ ሊጉ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የመዲናይቱ ክለብ የሆነው የካ ክፍለ ከተማ የ2017 የውድድር ዘመን ጨዋታዎቹን በምድብ ለ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ 8 ሰዓት ሲል ከንብ ጋር በመጫወት ጉዞውን ይጀምራል። ቡድኑም ራሱን ለማጠናከር ወደ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን በአዳዲስ መልኩ በማስፈረም ወደ አስራ አንድ ነባሮችን ውል ደግሞ በማደስ ለውድድሩ ተዘጋጅቷል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና አጥቂ እንዳለ ደባልቄ ፣ በፋሲል ከነማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን በተከላካይ ስፍራ ተጫውቶ ያሳለፈው ከድር ካይዲን ፣ በሀላባ ፣ ሀምበሪቾ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ስልጤ ወራቤ በአማካይ ቦታ ላይ መጫወት የቻለው ስንታየሁ አሸብር ፣ ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ያለፈውን ዓመት ደግሞ በቦዲቲ ከተማ የተጫወተው አማካዩ ውብሸት ወልዴ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እኣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተጫወተው አጥቂው እሱባለው ሙሉጌታ ፣ የደቡብ ፓሊስ ፣ ነቀምት ከተማ እና ካፋ ቡና አማካይ ዘሪሁን ይልማን ጨምሮ በግብ ጠባቂነት ቢኒያም ታከለ ከስልጤ ወራቤ ፣ ቴዎድሮስ አካሉ ከባቱ ከተማ ፣ እያሱ ተካ ከጅማ አባጅፋር ፣ ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሔር አማካይ ከጅማ ከኤሌክትሪክ ፣ ኤፍሱን በቀለ ተከላካይ ከሀላባ ከተማ ፣ ዳመነ ደምሴ ከሲዳማ ቡና አጥቂ ፣ ተመስገን ዙማ ከጅማ አባጅፋር ተከላካይ እና ሠለሞን ብሩ ተከላካይ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለክለቡ የፈረሙ አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ቡድኑ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የአቡበከር ሙራድ ተከላካይ ፣ ዘላለም ፍቃዱ ተከላካይ ፣ ንጋቱ ጌዴቦ ተከላካይ ፣ ወርቁ አዲስ ተከላካይ ፣ መስፍን ዳንኤል አማካይ ፣ ሚኪያስ አመሀ አማካይ ፣ ክብሮም ጽዱቅ አማካይ ፣ ካሳሁን ሰቦቃ አጥቂ ፣ ጁንዴክስ አወቀ አጥቂ ፣ ተካልኝ ገ/ስላሴ አጥቂ እና ሲሳይ ከበደ አጥቂ ውላቸውን ያደሱ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው።