በክስተቶች ታጅቦ በተካሄደው ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ሲዳማ ቡናን መርታት ችለዋል።
ሁለቱም ቡድኖች በመጨረሻው መርሃግብር ከተጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ የጀመሩት የመጀመርያው አጋማሽ ጥቂት የግብ ሙከራዎች፣ በቁጥር በርከት ያሉ ጥፋቶች እና ደካማ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች መገለጫዎቹ ነበሩ።
<a href=”https://www.betika.com/et/jackpot?utm_medium=display&utm_source=soccer-et&utm_campaign=display_et_acq_amh_sb_weekly-jackpot”><img class=”aligncenter wp-image-94475 size-full” src=”https://www.soccerethiopia.net/wp-content/uploads/2024/06/Aviator-Rain_900x90.png” alt=”” width=”900″ height=”90″ /></a>
ከተጋጣሚያቸው በአንፃራዊነት የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ባህርዳሮችም በዘጠነኛው ደቂቃ በሳጥን ውስጥ በቸርነት ጉግሳ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ቸርነት ጉግሳ መቶ ቶማስ ኢካራ መልሶበታል።
የጣና ሞገዶቹ ከደቂቃዎች በኋላም በተመሳሳይ ቦታ ፍፁም ዓለሙ ላይ በተሰራው ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም አምበሉ ፍሬው ሰለሞን መቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል።
ጥቂት የግብ ሙከራዎች በታዩበት አጋማሽ የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያደረጉት ባህርዳሮች ፍሬው ሰለሞን ከርቀት አክርሮ መቷት ከአግዳሚው በላይ ለጥቂት በወጣችው እና አምሳሉ ጥላሁን ከቆመ ኳስ ሞክሯት መክብብ ደገፉ ባወጣት ሙከራ ጎል ለማግኘት ጥረት አድርገዋል። በአጋማሹ በርከት ያሉ ጥፋቶች የተሰሩ ሲሆን ደስታ ደሙ እና ቶማስ ኢካራ ከሲዳማ ቡና አጥቂው አቤል ማሙሽ ደግሞ ከባህርዳር ከተማ ጉዳት አስተናግደው ተቀይረው ወጥተዋል።
በመጀመርያው አጋማሽ መጠነኛ ብልጫ የነበራቸው ባህርዳር ከተማዎች የተሻለ እንቅስቃሴ ባሳዩበት ሁለተኛው አጋማሽ በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ጉዳት ያስተናገደውን ቶማስ ኢካራን ተክቶ የገባው መክብብ ደገፉ ከበድ ያለ ጉዳት በማስተናገዱ ጨዋታው ወደ አስር የሚጠጉ ደቂቃዎች ተቋርጧል።
ጨዋታው ዳግም ከጀመረ በኋላም በስልሳ ሁለተኛው ደቂቃ ላይ በመጀመርያው አጋማሽ ፍፁም ቅጣት ምት ያመከኑት ሁለቱ ተጫዋቾች ተቀባብለው በማስቆጠር ባህርዳር ከተማን መሪ ማድረግ ችለዋል። ፍሬው ሰለሞን ፈጣኑ ቸርነት ጉግሳ ከመስመር ገፍቶ ወደ ሳጥን ይዟት የገባትን ኳስ ተቀብሎ ከመረቡ ጋር ያገናኛት ኳስም ቡድኑን መሪ ያደረገች ግብ ነበረች።
ከግቧ በኋላ ሲዳማ ቡናዎች ውስን መነቃቃት አሳይተው በሀብታሙ ታደሰ፣ መስፍን ታፈሰ እና ፍቅረ የሱስ ተ\ብርሀን ሙከራዎች ማድረግ ቢችሉም ተጨማሪ ግብ ያስቆጠሩት ግን ባህርዳር ከተማዎች ነበሩ።
ወንድወሰን በለጠ በጥሩ መንገድ በመስመር ይዟት ገብቶ ፍፁም ዓለሙ ወደ ጎልነት የቀየራት ኳስም የጣና ሞገዶቹ መሪነት ከፍ ያደረገች ነበረች።
<img class=”aligncenter size-full wp-image-87035″ src=”https://soccerethiopia.net/wp-content/uploads/2023/04/Gofere-900×110-1.jpg” alt=”” width=”900″ height=”110″ />
ሁለት የመከኑ ፍፁም ቅጣት ምቶች፣ አምስት ከባድ ጉዳቶች የተስተናገዱበት ጨዋታ በጣና ሞገዶቹ አሸናፊነት ሲገባደድ፤ ማክሰኞ የካቲት 23/2013 ዓ.ም በወሰኑ ዓሊ እና ፍፁም ዓለሙ ግቦች ሲዳማ ቡናን ሁለት ለአንድ ካሸነፉ በኋላ ላለፉት ስድስት የእርሰ በርስ ግንኙነቶች ሳያሸንፉ የቆዩት ባህርዳር ከተማዎች በቅርብ ዓመታት በሲዳማ ቡና የተወሰደባቸውን የበላይነት ቀልብሰዋል።