የጣና ሞገዶቹ ሲዳማ ቡናን 2ለ0 ረተው ወሳኝ ድል ካሳኩ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።
አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ
“ውጤቱ ይገባናል ፤ ሦስቱን ነጥብ በአሳማኝ ሁኔታ አሳክተናል ብዬ ነው የማስበው። ውጤቱ በቀላሉ የተገኘ አይደለም ብዙ መስዋዕት ተከፍሏል። ለተጫዋቾቼ ለቀጣይ ጨዋታዎች መነሳሳት ይፈጥራል። እንደዚህ ዓይነት ጨዋታዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው በዲኤስቲቪ ቢተላለፉ እላለሁ።”
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው – ሲዳማ ቡና
“ለምን ወረድ ያለ አቀራረብ ነበረን የሚለውን የምንገመግም ይሆናል። አጠቃላይ ዛሬ በነበረው እንቅስቃሴ ጥሩ አልነበርንም። የዝግጁነት እና የትኩረት ማነስ ነበር ፤ ተጫዋቾቼ ለተጋጣሚ ቡድን የሰጡት ግምት አነስተኛ የነበር ይመስለኛል።”