በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ መቻሎች በአብዱልከሪም ወርቁ ብቸኛ ጎል ድል ካደረጉበት መርሐግብር በኋላ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የድኅረ ጨዋታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል
“ይሄ ነጥብ ለእኛ በጣም ያስፈልገን ነበር ፤ ስለዚህ ተጫዋቾቼ የተሰጣቸውን ነገር በሙሉ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተዋል። ሁሌም እንደዚህ ናቸው ምክንያቱም የመቻል ተጫዋች ስትሆን ሁሌም ያለህን መስጠት አለብህ እንደዚህም ነው የሰጡት እና በጣም ደስተኞች ነን።”
አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
“የጨዋታው እንቅስቃሴ የመጀመሪያው 45 ቀስ በቀስ ማለትም ከመጀመሪያው ሃያ ደቂቃ በኋላ በኳስ ቁጥጥርም የግብ ዕድል በመፍጠርም የተሻለ አርባ አምስት ያሳለፍንበት ነበር። ያንን ደግሞ በሁለተኛው 45 በበለጠ ለማሻሻል ሙከራ አድርገናል ፣ ያም ተሳክቶልናል ግን የምናገኛቸውን የግብ ዕድሎች ሚስ ማድረጋችን ወይም ደግሞ የመጨረሻው የሜዳ ክፍል ላይ የምንሰራቸው ስህተቶች ጎል እንዳናገባ አድርጎናል እነርሱ ደግሞ ያገኟትን አጋጣሚ በመጠቀማቸው ጨዋታውን ሚስ ልናደርግ ችለናል።”