የምሽቱ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 2ለ0 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ ሶከር ኢትዮጵያ ከሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ጋር ቆይታ አድርጋለች።
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ
“በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች አካባቢ የመፍዘዝ ዓይነት ነገሮች ነበሩ ፣ ምንአልባት ትኩረት ማነስ እንዳይኖር ከመጀመሪያውም ቡድኑን ለማዘጋጀት እየሞከርን ትኩረት አድርገን ነበር። ጨዋታው ላይ በተፈጠረው ነገር ውጤቱ ሊቀየር ችሏል። ፔናሊቲ ነው አይደለም ሌላ ጉዳይ ነው ፤ ለዳኞች ለራሳቸው ልተው ግን ዳኛው ሳይወስን ነው ረዳቱ የወሰነው እና በዛ ብዙም ኮምፕሌን ማቅረብ አልፈልግም ፣ ምክንያቱም የእነርሱ ሥራ ነው ሥራቸውን ሠርተዋል።”
አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና
“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፣ ያለፉትን ጨዋታዎች በእንቅስቃሴም ጥሩ ሳንሆን ተሸንፈን ነበር። ነገር ግን ከዛ ነገር መውጣት እንዳለብን ተነጋግረን ነበር ፣ የሠራነው ሳይኮሎጂካሊ ልጆቻችንን ከነበርንበት እንዲወጡ ማድረግ ነበር ያሰብነው እና እግዚአብሔር ይመስገን ተሳክቶልን ጥሩ ነገር ሠርተናል።”