ወልዋሎ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በይፋ ተለያይቷል

በትናንትናው ዕለት በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጉዳይ ስብሰባ የተቀመጠው የወልዋሎ ቦርድ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ለመለያየት ወስኗል።

ሐምሌ 9 በይፋ የወልዋሎ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙትና ላለፉት ዘጠና አምስት ቀናት ክለቡን በማሰልጠን የቆዩት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከደካማው አጀማመር በኋላ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል። የወልዋሎ የቦርድ አባላት በትናንትናው ዕለት በአሰልጣኙ ጉዳይ ረዘም ላሉ ሰዓታት ከተወያዩ በኋላ ከአሰልጣኙ ጋር ለመለያየት ከውሳኔ ሲደርሱ በቀጣይ አሰልጣኝ ዙርያም አቅጣጫዎች በማስቀመጥ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴዎች ጀምረዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨምሮ መቻል፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ ማሰልጠን የቻሉት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በወልዋሎ የሦስት ወራት ቆይታ አድረገው አምስት ጨዋታዎች በማከናወን አምስት ሽንፈቶች ማስተናገዳቸው ይታወሳል።