በምሽቱ መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን አራት ጎሎችን በመቐለ 70 እንደርታ ላይ በማስቆጠር ካሸነፈ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን
“ጥሩ ነው። የጥሩ መገለጫው መቼም ማሸነፍ አንድ ነገር ነው ከዛ በላይ ደግሞ በአሸናፊነት ውስጥ ሆነህ ጎሎችን ማግባት ደግሞ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ከጎል ድርቅ ወደ አግቢነት ተሸጋግረናል ጥሩ ነው ለእኛ ትልቅ ነገር ነው።”
አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ
“ጨዋታው ከባለፈው ትንሽ የጥንቃቄ ጨዋታዎች ለመጫወት ነበር አስበን የገባነው። በዛ ላይ ከሽንፈት ለማገገም ነበር ሁሉን ነገራችንን ይዘን የገባነው ጨዋታው እኛ ባሰብነው ሳይሆን በተቃራኒ ሆነ ይሄ እግር ኳስ ነው ሊከሰት ይችላል።”