ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን በመርታት ተከታታይ ድሉን ካስመዘገበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
”እግር ኳስ ፕሮሰስ ነው። በእረፍት አንዳንድ የጎደሉን ነገሮች አሉ እነሱን እንሰራበታለን። ጠንካራ ጎናችን ህብረታችን ፣ ለስራ ያላቸው ታታሪነት፣ ያላቸው ፍላጎት እነዚህ ነገሮች ተዋህዶ ነው ውጤት ምመጣው።”
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
”ጨዋታው መጀመሪያ ላይ በጣም ቀላል ይመስል ነበር። አለማሸነፋችንን ተከትሎ ተጫዋቾች ላይ በራስ መተማመን ላይ ጥርጥር ያለ ይመስለኛል፣አንዳንድ ግዜ ስታሸንፍ ለራስህ የምትሰጠው የራስ መተማመን አለ። ነጥብ እስካልያዝክ በጣም ከባድ ነው።”