ዋልያዎቹ ከሣምንት በኋላ ለሚያደርጓቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ በጊዜያዊነት በሾማቸው በዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ፣ በምክትል አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና በግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ደሳለኝ ወልደጊዮርጊስ እየተመራ ሕዳር 7 ከታንዛኒያ እና ሕዳር 10 ቀን ደግሞ ከኮንጎ ዲ.ሪ ጋር ለሚያደርጋቸው የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 5ኛ እና 6ኛ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉ ታውቋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 23 ተጫዋቾች ማለትም
ግብ ጠባቂዎች
1. ሰዒድ ሀብታሙ – ሀዋሳ ከተማ
2. ፍሬው ጌታሁን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
3. ዐብዩ ካሣዬ – ድሬዳዋ ከተማ
ተከላካዮች
1. ያሬድ ባየህ – ሲዳማ ቡና
2. ፍሬዘር ካሳ – ባህር ዳር ከተማ
3. አሥራት ቱንጆ – ድሬዳዋ ከተማ
4. ራምኬል ጀምስ – ኢትዮጵያ ቡና
5. ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
6. አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
7. ዳዊት ማሞ – መቻል
8. ያሬድ ካሳዬ – ኢትዮጵያ መድን
አማካዮች
1. ሬድዋን ናስር – ሲዳማ ቡና
2. አብነት ደምሴ – ወላይታ ድቻ
3. ቢኒያም ዐይተን – አዳማ ከተማ
4. አብዱልከሪም ወርቁ – መቻል
5. አማኑኤል ዮሐንስ – መቻል
6. በረከት ወልዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አጥቂዎች
1. ቸርነት ጉግሳ – ባህር ዳር ከተማ
2. መሐመድኑር ናስር – ድሬዳዋ ከተማ
3. በረከት ደስታ – መቻል
4. አንተነህ ተፈራ – ኢትዮጵያ ቡና
5. ኪቲካ ጅማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
6. አማኑኤል ኤርቦ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከነገ ጥቅምት 28 ከ6፡00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።