ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኑ ስብስብ አንድ ተጫዋች ውጭ ሲሆን በምትኩ የሲዳማ ቡናው ተጫዋች ስብስቡን ተቀላቅሏል።
በአዲሱ ጊዜያዊ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እየተመሩ በመጨረሻዎቹ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች ለመሳተፍ በአዲስ አበበ ስታዲየም ልምምዳቸውን መስራት ከጀመሩ ሦስተኛ ቀናቸው ያስቆጠሩት ዋሊያዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አጥቂ ኪቲካ ጅማ ጥሪውን ተቀብሎ ብሔራዊ ቡድኑን የተቀላቀለ ቢሆንም አስቀድሞ ከነበረበት ጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ያላገገመ መሆኑን በመግለፅ መሄዱ ታውቋል።
ይህን ተከትሎ ተጫዋቹ ከስብስቡ ውጭ ሲሆን ቡድኑን በምትኩ የሲዳማ ቡናው አማካይ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን ጥሪ ተደርጎለት በዛሬው ልምምድ መሳተፍ ጀምሯል።
ሕዳር 7 ከታንዛንያ፤ ሕዳር 10 ደግሞ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ተጫውቶ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጉዞው የሚያገባድደው ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን በምድቡ አራት ጨዋታዎችን አከናውነው በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ዋልያዎቹ በውድድሩ አንድ ግብ አስቆጥረው ዘጠኝ ግቦች ማስተናገዳቸውም ይታወቃል።