በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ የተወከለችበት የካፍ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ በሞሮኮ ይጀመራል።
አራተኛው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ በዛሬው ዕለት በሞሮኮ ይጀመራል። በመክፈቻው ጨዋታ ቲፒ ማዜምቤ እና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ የሚገናኙ ሲሆን በምድብ ሁለት ቻምፒየንነታቸውን ለማስጠበቅ ወደ ውድድሩ ያቀኑት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ኤዶ ኩዊንስ እና በቅርቡ ስማቸውን ከቱታንክሃሙን ወደ ማሳር ከለወጡት የግብፅ ተወካዮች ጋር የተደለደሉት ንግድ ባንኮች በነገው ዕለት የውድድር የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በነገው ዕለት ከኤዶ ኩዊንስ፤ ረቡዕ ህዳር 4 ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ፤ ከሦስት ቀናት በኋላ ሕዳር 7 ደግሞ ከግብፁ ተወካይ ማሳር ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉት የምስራቅ አፍሪካ ቻምፒየኖቹ በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ በውድድር ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ውጤት
ከማስመዝገባቸው በፊት በሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደው በታላቁ የአፍሪካ ሴቶች የእግርኳስ መድረክ ሳይሳተፉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን የሴካፋ ቻምፒየን በሆኑበት ማግስት ኢትዮጵያን ወክለው በውድድሩ ይሳተፋሉ።