👉 “እንደነዚህ ያሉ ዕድሎች የሚደገሙበት ሁኔታ አይኖርም..
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ባሕሩ ጥላሁን በአሰልጣኝ መሳይ ውል እንዲሁም ክለብ እና ብሔራዊ ቡድን ደርቦ መሥራትን አስመልክቶ ምን አሉ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላለበት የምድቡ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አስመልክቶ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን በብሔራዊ ቡድኑ ጉዞ ጋር በተያያዘ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ከአስራ አንድ ወር በኋላ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተዋል። ከሚዲያ አካላትም የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሳላቸው ሲሆን በዋናነት
የአሰልጣኝ መሳይ የውል ዘመን እና አንድ አሰልጣኝ ብሔራዊ ቡድን እና ክለብን ደርቦ መስራት ከዚህ በኋላ ይኖራል ወይ ተብለው ሲጠየቁ
“የአሰልጣኝ መሳይ የውል ዘመን የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ተወያይቶ የወሰነው ከፊታችን ያሉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እና የሀገራት ዋንጫ(የቻን) ማጣሪያ ጨዋታዎችን በዋናነት እንዲሠሩ የተሰጠ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ ሌሎች ስራዎችን እንደሚሰሩ ጠቁመው የብሔራዊ ቡድን እና ክለብን ደርቦ አሰልጣኝ እንዲሰራ የተደረገበት ሁኔታ ሲያስረዱ “ይሄን ያደረግንበት መንገድ ገምግመን ተገቢ እንዳልሆነ አምነናል። ምክንያቱም ሁለት ስራ ደርቦ ሲሰራ አቅሙን በተገቢው መንገድ እዳይወጣ እና የተለያዩ ምክንያቶች እንዲነሱ ያደርጋል። ስለዚህ ከዚህ በኋላ በሚኖሩ የአሰልጣኝ ቅጥሮች እንደነዚህ ያሉ ዕድሎች የሚደገሙበት ሁኔታ አይኖርም።” ብለዋል