ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን ከረታበት ከምሽቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ አብዱ ቡሊ – አዳማ ከተማ
”ጨዋታው ጥሩ ነው። በቀይ ካርድ ተጫዋቾች እስከተወገዱበት ድረስ ባላንስ ነው የግብ እድሎችንም ፈጥረን ነበር። ያገኘነውን አጋጣሚ ያለመጠቀም ችግር ውጤቱን ቀይሮታል። አለመረጋጋት ታይቶብናል ማሻሻል ያሉብን ነገሮች አሉ። ሁለት ሶስት ሽንፈት ሊያጋጥም ይችላል ነገር ግን ከስህተቶቹ ምን ያህል ተምረናል የሚለው ነገር ነው እኔን ሚያሳስበኝ።”
አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን
”ማሸናፋችን ጥሩ ሆኖ በማሸነፍ ላይ ሆነን ብዙ ነገር ማስተካከል ይቻላል፣ ተሸንፈህ ከማስተካከል ይልቅ አሸንፈህ ማስተካከል አይከብድም። በዲስፕሊን በኩል ትልቅ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው። የአሸናፊነት ስነልቦና መመለሱ በራሱ አንድ ትልቅ ነገር ነው።”