“በዚህ ሃይ ኢንቴንሲቲ ጨዋታ እንደዚህ መጫወታቸው ደስ ብሎኛል።” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
“አንድ ነጥብ ይዘህ መመለስ ቀላል ነገር አይደለም።” አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ
ያለግብ ከተጠናቀቀው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
”48 ሰዓት ሳይሞላ ነው ሙሉ ለሙሉ የተጫወትነው፤ የሠራነው ልምምድ የለም ተጫዋቾቼን በዚህ አጋጣሚ ማመሰገን እፈልጋለሁ። በዚህ ሀይ ኢንቴንሲቲ ጨዋታ እንደዚህ መጫወታቸው ደስ ብሎኛል። ውጤቱ ሊያስከፋ ይችላል ፤ አለማሸነፋችን!”
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – ድሬዳዋ ከተማ
”ከባለፈው ጎል ላይ ቶሎ ቶሎ በመድረስ የተሻልን ነበርን። ውጤቱ እንደዚህ ሆኗል አንዳንዴ ኳስ ነው ያለውን ነገር መቀበል ግድ ይለናል። አራት ቡድን በሚወርድበት አንድ ነጥብ ብርቅ በሆነበት ጨዋታ ላይ አንድ ነጥብ ይዘህ መመለስ ቀላል ነገር አይደለም እና ጥንቃቄ እያደረግን ይሄንን ጨዋታችንን አሁንም እያሳደግን መሄድ ነው የሚጠበቅብን።”