”በአሸናፊነት ውስጥ ስህተቶች ፤ በተሸናፊነት ውስጥ ጥንካሬዎች ይኖራሉ።” አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ
”ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት እና ለሌላ ክለብ መጫወት አንድ አይደለም።” አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ
አዳማ ከተማዎች በስንታየሁ መንግሥቱ አማካኝነት ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ኢትዮጵያ ቡናን 2ለ1 ከረቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ አብዱ ቡሊ – አዳማ ከተማ
”ተከታታይ ስትሸነፍ በተጫዋቾች ላይ ጫና ስለሚመጣ ያ እንዳይሆን ተጫዋቾቹን የማነሳሳት ስራ ነበር። ያለፈው ቀይ ተጫዋች ጎሎብናል ቢኒያም ወጥቷል በእነዚህ ሁሉ ተጠጋግነን ያልኳቸውን ሰምተው ጥሩ ነገር ሠርተናል ደስተኛ ነኝ።”
አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና
”ጨዋታው በፈለግነው ልክ አይደለም የሄደልን። እንደተጀመረ ነው ጎል ያስተናገድነው። በተወሰነ መልኩ መረጋጋቶች አልነበሩም። መስተካከል ያለባቸው ነገሮች አሉ እሱ ላይ ማየት መቻል አለብን። ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት እና ለሌላ ቡድን መጫወት አንድ አይደለም። ጫናዎችን የመቋቋም ነገር ተጫዋቾች ላይ ከብዷል ግን መታገል ነው እነዚው ተጫዋቾች ናቸው ዓመቱን የሚጫወቱት።”