የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ምርጫ እንደ ተጠናቀቀ እየተነገረ ይገኛል፡፡
ከፌዴሬሽኑ ጊዜያዊ ፀሃፊና ህዝብ ግንኙነት እንደሰማነው ከመጨረሻዎቹ አምስት እጭዎች መካከል በቴክኒክ ኮሚቴው ውሳኔ መሰረት አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ መመረጣቸው ታውቋል፡፡
ፌዴሬሽኑ በቅርብ ቀናት ውስጥ አሰልጣኝ አጥናፉን በማነጋገር የደሞዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ሲደርሱ ማረጋገጫ ይሰጣል ተብሏል፡፡
አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ዋናው ብሄራዊ ቡድን የኤፊ ኦኑራ ረዳት በመሆን የሰሩ ሲሆን በኤሌክትሪክ የአሰልጣኝ ዮርዳን ስቶይኮቭ ረዳት ሆነው ቆይተው ከቡልጋርያዊው ስንብት በኋላ በዋና አሰልጣኝነት ሰርተዋል፡፡ በ2007 የውድድር ዘመን መባቻ ከኤሌክትሪክ የተሰናበቱት አሰልጣኝ አጥናፉ በአአ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ ክለብ የቴክኒክ አማካሪ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ቡድን በአንጎላ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ከግብጽ ጋር ያደርጋል፡፡