የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 0-1 ሀዲያ ሆሳዕና

“በዚህ ዓይነት ሁኔታ በሊጉ መቆየት የሚታሰብ አይደለም።” አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት

“ግብ ካልተቆጠረብን እንደምናገባ እርግጠኛ ነኝ።” አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ

ከጨዋታ ሳምንቱ የማሳረጊያ መርሐግብር መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ ተከታዩን ብለዋል።

አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት – ስሑል ሽረ

“ካለብን የተጫዋቾች ጉዳት አንፃር ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ ውጤቱ ግን የሚያስከፋ ነው። በዚህ አይነት ሁኔታ በሊጉ መቆየት የሚታሰብ አይደለም በቀጣይ ተጫዋቾቻችን ከጉዳት ተመልሰው በተሻለ የሜዳ ላይ ብቃት እንደምንመለስ ምንም ጥርጥር የለውም።”

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

“በመጨረሻ ካደረግናቸው ሁለት ጨዋታዎች አንፃር የዛሬው የተሻለ ነበር ፤ ግብ ካልተቆጠረብን እንደምናገባ እርግጠኛ ነኝ በመከላከሉ ረገድ በጣም ጠንካራ ነን።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link