ኢትዮጵያ ራሷን አግልላለች

ኢትዮጵያ በመጪው ታኅሣሥ 5 ሊጀመር ቀነ ቀጥሮ በተያዘለት ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል።

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከታኅሣሥ 5-18 ሊደረግ ፕሮግራም የወጣለት ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣርያ በሁለት ምድቦች ሊደረግ መርሐግብር ቢወጣለትም በምድብ 1 ተደልድላ የነበረችው ኢትዮጵያ ራሷን አግልላለች።

የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ለሴካፋ ባሳወቁት መሠረት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት ውድድሩ ላይ ሊሳተፍ አልቻለም።