የአሰልጣኞች አስተያየት | መቻል 4-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ

በግቦች ከተንበሸበሸው የምሽቱ መርሐግብር ፍፃሜ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል

“ያስቆጠርናት የመጀመሪያ ግብ የጨዋታውን ሂደት ቀይራዋለች ፤ ጥሩ እየሰራን ነበር ግቧ መቆጠሯ ደግሞ ይበልጥ ሞራል ሰጠን። በዘጠኝ ጨዋታ ስለዋንጫ ማውራት የዋህነት ነው ፤ ነገርግን ለዋንጫ የምንጫወት ከሆነ ሁሉን ጨዋታ በዛሬው ዓይነት የማሸነፍ ስሜት መጫወት አለብን። ”

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

“አጀማመራችን ጥሩ ነበር። ፍፁም ቅጣት ምት እስኪሰጥብን ድረስ ጨዋታው ጥሩ ነበር ነገር ግን ከፍፁም ቅጣት ምቱ በኋላ ተጫዋቾቼ በተወሰነ መልኩ ስሜታዊ ሆነው ነበር ይህን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ሁለተኛ ግብ አስተናግደናል። ፍፁም ቅጣት ምቷ የጨዋታውን ሂደት ቀይራዋለች።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link