ኢትዮጵያ ቡና ከሳምንታት ጥበቃ በኋላ ከድል የታረቀበት ጨዋታ መጠናቀቅን ተከትሎ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና
“ከተከታታይ ሽንፈቶች እንደመምጣታችን እንዲሁም ያለንበት ደረጃ ቡድናችንን የማይመጥን በመሆኑ በተወሰነ መልኩ ጥንቃቄ ለማድረግ ሞክረናል ፤ ከፈጣሪ ጋር ባሰብነው መንገድ ጨዋታው ሄዶልናል።”
አሰልጣኝ በረከት ደሙ – አርባምንጭ ከተማ
“ጨዋታው ከውጤት አንፃር ጥሩ አልነበረም ፤ በሁለቱም አጋማሾች ኳሱን በተሻለ መንገድ መያዝ ችለናል ፣ነገርግን ወደ ማጥቃት የምናደርገው ሽግግር ፍፁምነት የጎደለው ነበር ያም ወደ ጎል ይበልጥ ቀርበን ውጤታማ እንዳንሆን አድርጎናል።”