የአሰልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 3-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ባህር ዳር ከተማ ከአስደናቂ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጋር የዓምናውን ሻምፒዩን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከረቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ደግዓረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ
“ልጆቻችን በሙሉ የጨዋታ ጊዜ ያላቸውን 100 % ሰጥተው ተጫውተዋል ፤ ከጨዋታ ጨዋታ ቡድናችን ላይ እድገት እያየን ነው በተለይም የተገኙ የግብ ዕድሎችን ከመጠቀም አንፃር ያለብንን ክፍተት በተወሰኑ መልኩ የቀረፍንበት ጨዋታ ነበር።”

አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
“በጨዋታው አልተደሰትኩም ፤ ጥሩ አልነበርንም።እንደ አጠቃላይ የመከላከል አደረጃጀታችን መስተካከል ይፈልጋል።አምና ከነበረን ነገር አንፃር አሁን ያለንበት ሁኔታ እኛን የሚመጥን አይደለም።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link